”ወንድሜን በአምስት ጥይት በሳስተው ነው የገደሉት” ኪዳኔ ጌታቸው

በወልዲያ ከተማ በጥምቀት በዓል ማግስት የተከሰተውን ተቃውሞ ተከትሎ የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ በርካቶች ህይወታቸውን ማጣታቸው ይታወቃል። መንግሥት የሟቾች ቁጥር ሰባት ነው ቢልም ያነጋገርናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ግን የሟቾችን እና የቁስለኞችን ቁጥር ከፍ ያደርጉታል። ከከተማዋ ነዋሪዎች እንደሰማነው ከሟቾቹ መካከል አዛውንቶች እና እድሚያቸው በአስራዎቹ መጀመሪያ ላይ የሚገኙ ሁለት ታዳጊዎች ይገኙበታል። ከዚህ በተጨማሪ በጥምቀት በዓል ማግስት ከተገደሉት መካከል በወልዲያ ከተማ በብረታ ብረት ሥራው የሚታወቀው ገብረመስቀል ጌታቸው ይገኝበታል። ገብረመስቀል እድሜው ወደ 35 የሚጠጋ ሲሆን ባለትዳር እና የ5 ዓመት ሴት ልጅ አባት ነበር። ገብረመስቀልን በቅርብ የሚያውቁት ጠንካራ ሰራተኛ ስለመሆኑ ይመስክሩለታል። ብረመስቀል የብረታ ብረት ድርጅት የነበረው ሲሆን…

Read More