ከአንድ ቤት ሶስት ወንድማማቾች በአጋዚ ጥይት

ኦሮሚያ >>>>> የደም መሬት
ከአንድ ቤት ሶስት ወንድማማቾች በአጋዚ ጥይት 
ሺርካ, አሩሲ
Abbaa Joel

ይህን ዜና የሰማሁት ንጋት ከመኝታዬ ተነስቼ የኦሮሚያ ሜዲያ ኔትዎርክ (OMN) 
የ Facebook ገፅ በተመለከትኩበት ጊዜ ነበር። ገና የዜናውን እርዕስ ስመለከት ነበር ውስጤ መታመም የጀመረው። ከአንድ ቤት ሶስት ወንድማማቾች በትግሬው ታጣቂ ሃይል መገደላቸውን ይናገራል። የእልቂት ዜና መስማት የለመደው ጆሮዬ ይህንንም በሶስት ወንድማማቾች ላይ የተፈፀመ ወደር የለሽ ግድያ ለመስማት አላመነታም። እናም የሰለባዎቹ ቤተሰብ የሆኑ ወላጅ አባት አቶ ጀማልና ወላጅ እናት በታመመ አይምሯቸው ስለ ልጆቻቸው እልቂት የተናገሩትን በእንባ ታጅቤ (ለማልቀስ የፈጠረን ጉዶች ሆነናልና) ማዳመጥ ጀመርኩ።

ምስራቅ አርሲ በሽርካ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ሶስቱ ወንድማማቾች ባካባቢው ሰፍሮ የሚገኘው የአጋዚ ጦር ምንም ዓይነት ሃጥያት ሳይኖርባቸው ከተሰበሰቡበት መኖሪያ ቤት በማስወጣት ሁለት ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በራፍ ደጅ ላይ ጭካኔ በተሞላበት መልኩ ረሽነዋቸዋል። አቶ ጀማል ሁሴን የሟቾቹ ወጣቶች አባት ናቸው። በግብርና ስራ የሚተዳደሩ አባት ናቸው። እኚህ አባት ለ OMN ጋዜጠኛው ደመቀ ነጋሳ አይምሮዬ ልክ አይሰራምና በደንብ ላላወራህ እችላለው ብለው በሚናገሩበት ቃለ ምልልስ ላይ ልጆቼን ያለሃጥያታቸው ከጎኔ ነጠቁብኝ በማለት ይናገራሉ።

የልጆቻቸው ስም:-
1. ወጣት መረቡ ጀማል 
2.ወጣት ቶላ ጀማልና 
3.ወጣት አብዲሳ ጀማል የሚባሉ ናቸው።

አቶ ጀማልና ባለቤታቸው ልጆቻቸው በአሰቃቂ ሁኔታ ከተገደሉበት ሰዓት አንስቶ እራሳቸውን እንዳያጠፉ ሲባል ሁለት እጃቸው ወደኋላ ታስሮ በዘመድ አዝማድ እየተጠበቁ ነው። በተለይ የሟቹ እናት ብዙም ማውራት ካለመቻላቸው ባለፈ በጉሉኮስ በአልጋ ላይ እንደሚገኙም ነው የታወቀው።

ከአንድ ቤተሰብ ሁለት ልጆችን ማጣት አሁን አሁን የተለመደ ቢሆንም በአቶ ጀማል ሶስት ልጆች ላይ የተፈፀመው ግድያ ግን የመጀመሪያ ሊባል የሚችል ነው። ኦሮሚያ በልጆቿ ደም ጨቅይታለች። የሚደርስላት ከማውራት ባለፈ ፈጥኖ አለሁልሽ የሚላት አካል አጥታለች። ህዝቦቿ ለመስዋዕትነት እንደሚቀርብ በግ እየታረዱ ነው። ጩኸቱ ዋይታው በያንዳንዱ ጎጆ ይሰማል። አንድ ፣ ሁለት ወይንም ሶስት ልጆቹን በጥይት የተቀማ ቤተሰብ በየመንደሩ ማየት በጣም ቀላል የሆነበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።

አቶ ጀማል በኦሮምኛ ቋንቋ ከ OMN ጋር ያደረጉትን ቆይታ ሙሉ ለሙሉ በአማርኛ ተርጉሜ የማቅረብ ትዕግስቱ የለኝም። ምናልባት ለአማርኛ ሰሚዎች በድጋሜ በአማርኛ ክፍለ ጊዜ ኦ ኤም ኤኖች ያቀርቡታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። የአቶ ጀማልንም ሆነ የባለቤታቸውን ድምፅ መስማት በራሱ ህመም ነው።

በመጨረሻም የኦሮሞ ህዝብ የሚያወራለት ሳይሆን ታጥቆ የሚዋጋለትና የሚያዋጋው ሃይል ይፈልጋል። የራሳችንን ልጆች እሬሳ የሚያስቆጥረን ሳይሆን የጠላትን እሬሳ የሚቆጥርልን ቆራጥ የኦሮሞ ታግሎ አታጋይ ያስፈልገናል።

ወሬ ይብቃ!